ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
@eotcbook

ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍትን በPDF እና ተከታታይ ኮርሶችን ያግኙ
324  
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2019-04-27 

ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ( የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ). ፡. BGK ዘተዋሕዶ. ፡

1 ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ።
2 ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥
3 ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።
4 እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤
5 ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።
......
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-12-25 

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ሦስት. ፡. #ONEምዕራፍ. ፡. 1 አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።

2 ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።
3 አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።
4 በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ፥ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።
5 እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።
6 ከሚከብቡኝ ከአእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
7 ተነሥ፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።
8 ማዳን የእግዚአብሔር ነው፥ በረከትህም በሕዝብህ ላይ ነው።
@BGKZetewahdo
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-12-24 

#መልካም_እረኛ_እኔ_ነኝ. ዩሐ 10:14. ፧. ❇️ይህን ርዕስ በማንሳት በ29/03/11 የዕለቱን ወንጌል ሰለ ኖላዊ ትምህርት ሰጥቸ ነበር ፤ ከተጠቀምንበት በማለት ወደ ጽሑፍ ቀየርኩት.....

🔘በተነሳው ርዕስ ላይ ሁለት ነገሮችን እናገኛለን #መልካም_እረኛ እና #እኔ_ነኝ የሚሉ ሰፊ ርዕሶች።
🔘ለስም አጠራሩ ክብር ምሰጋና ይሁንና ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በዩሐንሰ ወንጌል ብቻ #እኔ_ነኝ እያለ ያስተማራቸው ትምህርቶች አለ። እነርሱም 6 ናቸው። በአጭሩ አሰቀምጠናቸው ስናልፍ፦
1⃣. " ኢየሱስም እንዲህ አላቸው።። #የሕይወት_እንጀራ_እኔ_ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።"(ዮሐ6:35)..እርሱ የሕይወት እንጀራ ነው እኛ እንበላለን ፤ በመብላችንም ዘላለማዊ እንሆናለን።
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 6)
----------
53፤ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።
54፤ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።
55፤ ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።
56፤ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
2⃣. " ደግሞም ኢየሱስ። #እኔ_የዓለም_ብርሃን_ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።"(ዮሐ 8:12)...እርሱ እውነተኛ ብርሃን እኛ ደግሞ በእርሱ ብርሃን ብርሃን ሆነን ለዓለም እናበራለን።
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5)
----------
14፤ #እናንተ_የዓለም_ብርሃን_ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
15፤ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
16፤ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ #ብርሃናችሁ_እንዲሁ_በሰው_ፊት_ይብራ።
3⃣. " #በሩ_እኔ_ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።"(ዮሐ10:9)...በክርሰትና ከክርስቶስ ውጭ #የሕይወት_በር የለም። በዚህ ሕይወት በር ከገባን በኋላ ከሕይወት በር እንዳንወጣ እንድሁም መውደቃችን መነሳታችን አይተው የሚራዱን ብዙ ቅዱሳን አሉ ነገር ግን የከበረች በረከታቸውን እርዳታቸውን ለማግኛት ቅድሚያ የሕይወት በርን አውቆ መግባትና መኖር ይገባል። በአጭሩ ይህ #የሕይወት_በር_ምንድን_ነው? ለምትሉኝ አባቶች #በሰይፍ_የተዘጋች_ገነት_በሰይፍ_ተከፈተች እንዳሉን የሕይወት በሩ #በሰይፍ_የተወጋው_ግራ_ጎኑ ነው። ይህ በር ነው የሕይወት ምንጭ...በዚህ በር ለማለፍ በሩ ላይ ያለውን ቅድሚ መቀበል ይቀድማል። በሩ ላይ #ደምና_ውሃ አለ። በደሙ ተገዝተን በውሃው ነጽተናል። " ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም #በክቡር_የክርስቶስ_ደም_እንደ_ተዋጃችሁ_ታውቃላችሁ።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:18-19)
4⃣. " #መልካም_እረኛ_እኔ_ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።"(ዮሐ10:14-15)
⏺ይህ መልካም እረኛ ሰለሚወዳቸው በጎች የሚሞት ነው። ይህን ለመረዳት ሶስቱን የጌታችን የእረኝነት ሰሞች እንመልከት፦
❇️#መልካም_እረኛ
" መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።"(ዮሐ10:11)
👆👆👆ይህ ሰለሚወዳቸው በጎች በፈቃዱ #ስለሚሞተው_ሞቱ የሚናገር ነው (ምዕራፉን ሙሉውን ያንብቡት)
❇️ #ታላቅ_እረኛ
" በዘላለም ኪዳን ደም #ለበጎች_ትልቅ_እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥"
(ወደ ዕብራውያን 13:20)
👆👆👆👆ይህ ሰለ ትንሳኤው የሚናገር ነው ተወዳጆች ያሰተውሉ።
❇️ #የእረኞች_አለቃ
" የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:4)
👆👆👆ይህ ሰለ ዳግም ምጽአቱ የሚናገርበት ነው።
✅ ይህን ጠቅለል ሰናደርገው ሶስቱም ሰሞቹ የሚናገሩት ሰለ በጎች የተደረገውንና የሚደረገውን ነው። ሰለዚህ እረኛው ለበጎቹ ይህን ካደረገ እኛም ለእረኛው እንመች።
5⃣. " ኢየሱስም። #ትንሣኤና_ሕይወት_እኔ_ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤"(ዮሐ11:25)
🔸ይህ ምሰጢር የሚታመን ወደፊት ከሚፈጸሙ አንዱ ነው።
6⃣. (የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 15)
----------
1፤ #እውነተኛ_የወይን_ግንድ_እኔ_ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።
2፤ ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
3፤ እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤
4፤ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።
5፤ #እኔ_የወይን_ግንድ_ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
➡️እኛ ቅርጫፎች ነን ለማለምለም ከግንዱ ጋር መጣበቅ ለመድረቅ ከግንዱ መውደቅ ወይም መቆረጥ ይጠበቅብናል። ይህ ነጻ ፈቃዳችን ነው ገር ግን ግንዱ ላይ ሆኖ አለማለምለም አልፎም አለማፍራት አይቻልም። ከግንዱ ስር የሚቆርጥ ምሳር አለ " #አሁንስ_ምሳር_በዛፎች_ሥር_ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።"(የማቴዎስ ወንጌል 3:10) ሰለዚህ በእውነተኛ ልንመላለሰ ግደታችን ነው።
ትምህርቱ እዚህ ላይ አላቆመም ፥ በዚሁ ምዕራፍ እውነተኛ እረኛ ምን ያደርጋል የሚለው ይቀጥላል...
☑️መንፈሳዊ ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇👇👇
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
📜 @zorthdox 📜
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
📜 @Hesychasm 📜
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
:
:
✅ ለመንፈሳዊ ጥያቄዎ
✅ ለመንፈሳዊ ውይይት
✅ ለአስተያየተዋ
👇👇👇👇👇👇👇👇
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Apophatism ፧፧፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
፧፧፧ @Archeanarchos ፧፧
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-12-09 

2018-11-01 

በቅርብ ቀን ይጠብቁን. ሰላም የገጻችን ተከታታዮች ከባለፈው አመት ሰኔ ጀምሮ የተቋረጠው እና ሲተላለፍ የነበሩ መርሃግብሮች በአዲስ መልክ በቅርብ ቀን ማቅረብ የምንጀምር መሆኑን ስንገልጽ መንፈሳዊ ደስታ ይሰማናል!

ሁላችሁም የሚቀርቡ መርሃግብሮችን እንድትከታተሉ በክርስቶስ ፍቅር እንጠይቃለን!
@BGKZetewahdo
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-09-16 

✍ ዘፍጥረት ምዕራፍ ሁለት አጭር ምልከታ. 🔘 ለሰው ልጅ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ማዘጋጀቱን ያሳያል. ➡️ የዕረፍት ቀን ከቁ 1-3

➡️ ምቹ ቦታ ቁ 4 ,15
➡️የሚያጠግብ መብል ቁ 5,9
➡️ ተስማሚ ሥራ ቁ 15
➡️ ተገቢ ሥልጣን ቁ 19,20
➡️ አስደሳች አጋር(እረዳት) ቁ 18-25
➡️ ነጻ ፈቃድ ከምርጫ ጋር ቁ 9,16,17
✝✝✝✝✝✝✝✝
✝ ምልከታ ✝
✝✝✝✝✝✝✝✝
✍ ከዘፍ 2:4 እ ስከ ዘፍ 3:24 ድረስ ፦
👉 በእነዚህ ሁለት ምዕራፍ ወይንም በ49 ቁጥሮች ውስጥ የ ፈጣሪን ስም ስናጠና "እግዚአብሔር አምላክ" በሚል 24 ጊዜ ተጽፏል። ነገር ግን በዚሁ ጥቅ ስ ው ስጥ ማለትም ከዘፍ 3:2-6 በ4ቱ ቁጥሮች ወይንም በሔዋንና በእባብ በተመሠለው በሰይጣን ንግግር ውስጥ "ሁለት ስህተቶች" እናገኛለን። አስተውሉ ተወዳጅ ፦ አስቀድሞ "እግዚአብሔር አምላክ" ተብሎ የተጻፈው በሁለቱ ንግግር ላይ "አምላክ"የሚለውን ቀንሰው "እግዚአብሔር" የሚለውን ብቻ ነው የተጠቀሙት ፤ ይህ ደግሞ የሰይጣን ሀሳብ ነው ፤ ሔዋንም አምላክነቱን እረስታ"እግዚአብሔር" የሚለውን ብቻ እንደ ሰነፍ ተማሪ ተጠቀመች። በመቀጠልም "የበስበስ ዝናብ አይፈራም" እንደሚባል ዘፍ 2:17 ላይ "ዛፍን አትብላ" በሚለው ቃል ላይ "አትንኩትም" ዘፍ 3:4 በውይይታቸው ላይ ጨምራ አወራች....የማረሳሳት ውጤት ይሏችኃል ይህ ነው።
✝ ከእግዚአብሔር ፍርድ ላይ ዘፍ 3:10-21
➡️ በመጀመርያ አስቀድሞ በዘፍ 2:23-24 ሴት ትባል የነበረችው ከ7 ዓመት ከ2ወር ከ17 ቀን በኊላ ከፍርዱ ቃል ላይ ተነስቶ "ሄዋን" አላት ዘፍ 3:20 (አስተውሉ ከዚህ በፊት ይህን ስም አልተጠራችበትም)
➡️ አዳምና ሔዋን የጸጋ ልብሳቸውን ካጡ በኃላ የለበሱት የበለስ ቅጠል ነበር ዘፍ 3:8 ፤ ከፍርዱ በኃላ ግን እግዚአብሔር በዘፍ 3:21 "የቁርበት ልብስ" አለበሳቸው። /አስተውሉ የለበሱት ቁርበት ወይም ቆዳ ከምንም ይሁን ደም ፈሶ ነው ፤ ይህ ደግሞ ትንሽ ፍንጭ ይስጠናል "ደም ሳይፈስ ስርየት ያለም ዕብ 9:23 /
⏺ የሰዋች እይታ
⏩ ብዙዋች ከፍርዱ ቃል ላይ ተነስተው ሴቶች በየወሩ የሚፈሳቸውን የወር አበባ ከእርግማኑ ጋር እንድሁም በወንዶች አንገት ላይ የሚገኛውን ማንቁርት ዕፅ በለሱን ስላልዋጠው ነው የሚሉ አሉ ይህ ግን ከእውነታ የራቀ ነው።
▪️እስኪ የት ላይ ነው ቅጠሉን እንደቆረሽ ያንችም ደም በየወሩ ይፍስስ ተብሎ የተነገረው....ጭንቅሽን አበዘዋለሁ የሚለው ከዚህ ጋር ምን አገናኛው......እሽ ይሁን እንበልና እነዚህን ሰወች እንድህ ብለን እንጠይቃቸው ፤ ፍርድ ከሆነ ለምን ከ15 ዓመት ጀምሮ 45 ዓመት ላይ ያቆማል ፤ ምክንያቱም የወር አበባ የሚያዩት በዚህ አመት ነውና
▪️ደግሞስ የወር አበባ የማታይ ሴት ትወልዳለችን ? ለመውለድ አስፈላጊ ከሆነ ልጅ የፍርዱ ውጤት ነውን.....ስለዚህ ይህ ከአፈታሪክ ያልዘለለ ነው።
:
✅ ወንድሞች እህቶች ይችን ቻናል ይጠቀሙባት ዘንድ ትጋብዧቸው ዘንድ እንማልዳችኃለን
:
መንፈሳዊ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
:
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @zorthdox 🔘 🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @Hesychasm 🔘
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
:
☑️ለመንፈሳዊ ጥያቄዋና አስተያየት
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
🎴 🎴
🎴 @Apophatism 🎴
🎴 @Archeanarchos 🎴
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-09-14 

⏹ኦርቶዶክሳዊ የቻናላችን መጠርያ ትርጉም እንገራችሁ. : : ⏹ለዚህ መነሻው መንፈሳዊ ወንድሞችና እህቶች በውስጥ መስመር የኦርቶክስ ነው ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ስለበዙ እርሱንም ለማሳወቅ ነው። መንፈሳዊ ቻናላችን *⃣የኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ሲሆን

🔹የቤተ ክርስቲያን ዶግማዋን/Doctrine/ ፣
🔹ቀኖናዋን/Canon/ እና
🔹 ትውፊቷን /Holy Tradition/ ጠብቆ ቅዱሳን አባቶች የአስተማሩን አብነት አድርገን፦
:
▶️በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን በአጭሩ እናጠናለን ፣
:
▶️የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቆዋችን እንመልሳለን ፣
:
▶️መንፈሳዊ ግጥሞችና ሌሎችንም ያስተምራሉ የምንላቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችን እንለቃለን።
:
:
:
*⃣ ከቻናላችን ጋር የተያያዙ ስሞችንና ትርጉማቸው
:
:
:
🔘Apophatism/አፓፍቲዝም/
:
✅ስለእግዚአብሔር ከምንገልጸው በላይ የማንገልጸው ይበዛል ማለት ነው። ይኸውም በሶስት ነገር ይገለጻል፦
1. የእግዚአብሔር ባሕርይ አይታወቅም ፤ አይመረመርም
2. የሰው ቋንቋ ነገረ እግዚአብሔርን በምልዓት መግለጵ አይችልም
3. ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በምልዓት መግለጽ አንችልም
:
:
*⃣እግዚአብሔርን የምናውቀው አለማወቃችንን በመግለጽ ነው። ቅዱሳን እየበቁ ሲሄዱ ዝም የሚሉት ለዚህ ነው። ዝም ማለታቸው የመደነቃቸው ብዛት ነው።
:
:
🔘Archeanarchos/አርኬ አናርኮስ/
:
:
✅እግዚአብሔር መጀመርያ የሌለው መጀመርያ ነው ማለት ነው። ዩሐ 1፡1
:
:
🔘Hesychasm/ሄሲካዝም/
:
✅ክርስቶስን ማዕከል በማድረግ እንድሁም ክርስቶስን ለብሶና መስሎ መመላለስ ፣ በጽሞና ድምጽ ሳያሰሙ መጸለይ ፣ ተፈጥሮን በሚያሸንፍ በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ መኖር ማለት ነው።
"ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት" ሮሜ 13፡14
:
:
:
🔘Shalom/ሻሎም/
:
✅ሰላም ለእናንተ ይሁን ፤ ሰላም ማለት ነው።
"ሰላምን እተውላችኃለሁ ፥ ሰላሜን እስጣችኃለሁ ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም" ዩሐ 14፡27
:
:
:
⏺ መንፈሳዊ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
▶️ የሕይወት መጽሐፍን እንካፈል ፤
▶️በመንፈሳዊ ግጥሞችና ጽሑፎችም ቃሉን ከመልዕክቱ ጋር እንረዳ።
:
:
♦️መንፈሳዊ ቻናላችን
:
➡️ ቃልህ እውነት ነው /ዘኦርቶዶክስ/
➡️ አይዋሽም መስቀሉ
:
:
▶️ ቻናሉን ለመቀላቀል
👇👇👇👇መንካት ብቻ
:
⏹ኦርቶዶክሳዊ የቻናላችን መጠርያ ትርጉም እንገራችሁ
:
:
⏹ለዚህ መነሻው መንፈሳዊ ወንድሞችና እህቶች በውስጥ መስመር የኦርቶክስ ነው ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ስለበዙ እርሱንም ለማሳወቅ ነው። መንፈሳዊ ቻናላችን *⃣የኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ሲሆን
🔹የቤተ ክርስቲያን ዶግማዋን/Doctrine/ ፣
🔹ቀኖናዋን/Canon/ እና
🔹 ትውፊቷን /Holy Tradition/ ጠብቆ ቅዱሳን አባቶች የአስተማሩን አብነት አድርገን፦
:
▶️በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን በአጭሩ እናጠናለን ፣
:
▶️የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቆዋችን እንመልሳለን ፣
:
▶️መንፈሳዊ ግጥሞችና ሌሎችንም ያስተምራሉ የምንላቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችን እንለቃለን።
:
:
:
*⃣ ከቻናላችን ጋር የተያያዙ ስሞችንና ትርጉማቸው
:
:
:
🔘Apophatism/አፓፍቲዝም/
:
✅ስለእግዚአብሔር ከምንገልጸው በላይ የማንገልጸው ይበዛል ማለት ነው። ይኸውም በሶስት ነገር ይገለጻል፦
1. የእግዚአብሔር ባሕርይ አይታወቅም ፤ አይመረመርም
2. የሰው ቋንቋ ነገረ እግዚአብሔርን በምልዓት መግለጵ አይችልም
3. ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በምልዓት መግለጽ አንችልም
:
:
*⃣እግዚአብሔርን የምናውቀው አለማወቃችንን በመግለጽ ነው። ቅዱሳን እየበቁ ሲሄዱ ዝም የሚሉት ለዚህ ነው። ዝም ማለታቸው የመደነቃቸው ብዛት ነው።
:
:
🔘Archeanarchos/አርኬ አናርኮስ/
:
:
✅እግዚአብሔር መጀመርያ የሌለው መጀመርያ ነው ማለት ነው። ዩሐ 1፡1
:
:
🔘Hesychasm/ሄሲካዝም/
:
✅ክርስቶስን ማዕከል በማድረግ እንድሁም ክርስቶስን ለብሶና መስሎ መመላለስ ፣ በጽሞና ድምጽ ሳያሰሙ መጸለይ ፣ ተፈጥሮን በሚያሸንፍ በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ መኖር ማለት ነው።
"ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት" ሮሜ 13፡14
:
:
:
🔘Shalom/ሻሎም/
:
✅ሰላም ለእናንተ ይሁን ፤ ሰላም ማለት ነው።
"ሰላምን እተውላችኃለሁ ፥ ሰላሜን እስጣችኃለሁ ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም" ዩሐ 14፡27
:
:
:
⏺ መንፈሳዊ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
▶️ የሕይወት መጽሐፍን እንካፈል ፤
▶️በመንፈሳዊ ግጥሞችና ጽሑፎችም ቃሉን ከመልዕክቱ ጋር እንረዳ።
:
:
♦️መንፈሳዊ ቻናላችን
:
➡️ ቃልህ እውነት ነው /ዘኦርቶዶክስ/
➡️ አይዋሽም መስቀሉ
:
:
▶️ ቻናሉን ለመቀላቀል
👇👇👇👇መንካት ብቻ
:
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @zorthdox 🔘 🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @Hesychasm 🔘
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
:
☑️ለመንፈሳዊ ጥያቄዋና አስተያየት
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
🎴 🎴
🎴 @Apophatism 🎴
🎴 @Archeanarchos 🎴
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-08-30 

🔘 ክፍል አራት ፦የቅዱሳት መጻሕፍት አቆጣጠር. : : ⏺ በክፍል ሶስት ከላይ ከተዘረዘሩት 60 የብሉይ ኪዳን ቅዱሳት መጻኅፍት መካከል የሚከተሉት ደግሞ ራሳቸዉን ችለዉ የማይቆጠሩት ናቸዉ ፡፡

🔹መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ( ከቀዳማዊ ሳሙኤል ጋር አብሮ ይቆጠራል)
🔹መጽሐፉ ነገስት ካልዕ ( ከቀዳማዊ ነገስ ጋር አብሮ ይቆጥራል )
🔹ጸሎተ ምናሴ ( 2 ዜና መዋዕል ጋር ይቆጠራል ምዕ 33 ቁ14 ይመልከቱ)
🔹መጽሐፈ ነህምያ ( ከመጸሐፈ ዕዝር ጋር አብሮ ይቆጠራል )
🔹መጽሐፈ ዕዝር ካልዕ ( ከዕዝር ሱቱኤል ጋር ይቆጠራል )
🔹ተረፈ አስቴር ( ከመጽሐፈ አስቴር ጋር ይቆጠራል )
🔹መጽሐፉ መቃቢያን ሳልስ ( ከመቃብያን ካልዕ ጋር አበይ ይቆጠራል)
🔹ሰቆቃው ኤርምያስ፣ተረፈ ኤርምያስ.....
:
▶️ሙሉውን ለማንበብ
👇👇👇ቤተሰብ ይሁኑ
:
:
:
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @zorthdox 🔘 🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @Hesychasm 🔘
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
:
☑️ለመንፈሳዊ ጥያቄዋና አስተያየት
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
🎴 🎴
🎴 @Apophatism 🎴
🎴 @Archeanarchos 🎴
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-08-30 

🔘 ክፍል ሶስት. ➡️ ብሉይ ኪዳን መጻህፍት. ✍ ብሉይ ኪዳን ቅዱሳት መጻህፍት ብዛታቸዉ 60/ስድሳ/ ናቸዉ፡፡ እነዚህም የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

:
:
▶️ ሙሉውን ለማንበብ
👇👇👇 ቤተሰብ ይሁኑ
:
:
:
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @zorthdox 🔘 🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @Hesychasm 🔘
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
:
☑️ለመንፈሳዊ ጥያቄዋና አስተያየት
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
🎴 🎴
🎴 @Apophatism 🎴
🎴 @Archeanarchos 🎴
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት
2018-08-29 

± መጽሐፍ ቅዱስ ሥዕላትን ይፈቅዳልን ???±. በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ የሚመለከት

ሰው እጅግ የተዋቡ የጌታችን ፣ የድንግል ማርያም ፣
የመላእክትና የቅዱሳን ሰዎች ሥዕላት ቤተ መቅደሱን ሞልተውት
ያገኛል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን በሥዕላቱ ፊት ዕጣን ሲያጥኑ ፣
መብራት ሲያበሩ ፣ ሲሳለሙና ሲሰግዱ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ
ደግሞ ‹ይኼ እኮ ጣዖት አምልኮ ነው!› ‹‹በላይ በሰማይ ካለው
፤ በታች በምድርም ካለው ከምድርም በታች በውኃ ካለው
የማናቸውንም ነገር ምሳሌ ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው
አታምልካቸውም›› ተብሎ በዐሠርቱ ትእዛዛት ላይ ተጽፎ
የለምን? ብለው ይከራከራሉ፡፡ (ዘጸ. 20፡4)
በእርግጥም እግዚአብሔር በሰማይም ፣ በምድርም ፣ ከምድርም
በታች ባሉ በማናቸውም ነገር የተቀረጸ ምስል አታድርግ ብሎ
በግልጥ ማዘዙ ማስተባበያ የሌለው እውነት ነው፡፡ ታዲያ
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህ ትእዛዝ በግልጥ ተጽፎ ካለ
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ካሉ የመላእክትን ፣
በምድር ካሉ የቅዱሳን ሰዎችን ሥዕላት ለመቅረጽም ሆነ
ለመሳል እንዴት ደፈረች? እውነት ይኼንን በግልጥ የተቀመጠ
ሕግ እያየች ሥዕላትን ለማዘጋጀት ምን አነሣሣት? የሚለው
ጥያቄ የግድ መመለስ ያለበት ነው፡፡
▶️ ሙሉውን መልሱን ለማንበብና ለመረዳት
👇👇👇 ቤተሰብ ይሁኑ!!!"
:
:እነዚህን ቻናሎች ይቀላቀሉ
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @zorthdox 🔘 🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
🔘 🔘
🔘 @Hesychasm 🔘
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘
:
☑️ለመንፈሳዊ ጥያቄዋና አስተያየት
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴
🎴 🎴
🎴 @Apophatism 🎴
🎴 @Archeanarchos 🎴
🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴🎴