💞#ትርታየ💞. ክፍል 22. ወዲያውም ፖሊሶች በሩን በርግደውት ገቡ ያሉትንም ሁሉንም አፋፍሰው ይዘዋቸው ሄዱ........

መቅደስና ጌዲዮን መናፈሻው ውስጥ ተቃቅፈው ለብዙ ሰአት አልወጡም መቅደስ የቆሰለውን ፊቱን እየደባበሰች አይን አይኑን ታየዋለች እሱ ግን የወይንሸት ነገር አሳስቦታል በርግጥ መቅደስም በውስጧ እየተመላለሰችባት ነው ቡሀላም ጌዲ አለችው እሱም ወዬ መቅዲ ሲላት ትላንት ስታገት እኮ ወይንሸትም አብራ ታግታላቸ በዛ ላይ እስካሁን አልመጣችም እኔ ፈራሁ አለችው ወይና ስልክ ደውላም እንደነገረችው ቡሀላም መረጃ አቀብላ እንዳስፈታችው ለማንም እንዳይናገር በራሷ በመቅደስ ነው ያስማለችው
....ለምን አትደውዪላትም አላት አረ ብዙ ሞክረናል ስልኳ ዝግ ነው አሁንም ሞክሪ ከፍታው ይሆናል አላት ስልኳን አውጥታ ደወለች ዝግ ነው ደግማ ደጋግማ ሞከረች ቢያንስ አስሮ ከሞከረች ቡሀላ ጠራ መቅደስ ከተቀመጠችበት ተነሳች ጌዲዮን በተስፋ ያዳምጣት ጀመር ስልኩ ተነሳ ሄሎ....ሄሎ....ሄሎ.....ወይና የት ነሽ አለቻት ወይናም በሚቆራረጠው ድምጿ ከክሊኒክ እየወጣች ቢሄንም እዚሁ ነኝ እየመጣሁ ነው አለቻት መቅደስም ግን ደናነሽ ስትላት አዎ ብላ ዋሸቻት ከ15 ደቂቃ ቡሀላም ግቢ እንደምትመጣ ነገረቻትና ስልኩን ዘጋችው ጌዲዮም ችግር አለ አላት መቅደስም ድምጿ ጥሩ አይደለም ግን ደናነኝ ብላኛለች አለችው በቃ አትፍሪ ደና ትሆናለች ዶርም ሄጄ ልብሴን ቀያይሬ እመጣለሁ ሲላት ወይና እየመጣች ስለሆነ እኔ እዚሁ እጠብቅሀለሁ አለችው ግንባሯን ስሟት ሄደ።
.........ባለቻት ደቂቃ ወይና ግቢ ገባች መቅደስ ስታያት ደነገጠች ፊቷ ድልዝ ብልዝ ብሎ አልኮን ተቀብቷል አይኗ ገብቷል ጉንጯ ደግሞ አብጧል ጭራሽ ያቺ ቀበጧን ወይንሸት አትመስልም መቅደስ አቅፋ ምን እንደሆነች ጠየቀቻት ወይና ግን መልሷ ምንም አልሆንኩምው ነበረ ብዙ ለመነቻት ፍንክች ዮናስ ነው አይደል ዝም መቅደስ ተናደደች እንዴ ፊትሽ እንደዚህ ባንዲራ መስሎ የምንብምንም አልሆንኩም ነው አለቻት ወይና አይኗ ግንባ ሞላ መቅዲ ይሄ ይገባኛል እንደውም እንደኔ በደል ሲያንሰኝ ነው አለቻት መቅደስ ግራ ገብቷት የተፈጠረውን እንድትነግራት ባባቷ ስም ለመነቻት እሷም ቤተክርስቲያ ሄደው እንደምትነግራት ቃል ገብታ ይዛት ሄደች......
.......ከቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እንደገቡ ከጥላ ስር ቁጭ አሉ ወይና ከመጀመሪያ ቀን አንስቶ እስከዛሬ ያረገቻትን በንባ ጎርፍ እየታጠበች ነገረቻት ይህን ሁሉ ያረገችውም አባቷን ለማሳከም እንደሆነ እናም በግዚያብሄር ስም ይቅርታ እንድታደርግላት ከግሯ ተንበርክካ ለመነቻት መቅደስ ግን የሰማችውን ማመን ስለተሳናት ቃል ሳተነፍስ ጥላት እየተጣደፈች ወጣች አጋጣሚ ሆኖ የለቱ ጉባኤ የስብከት ፕሮግራም ላይ ደርሶ ነበር የስብከቱም ቃል ይቅር እንዳልኳችሁ ይቅር ተባባሉ ነው መቅደስ ይህን ቃል ስትሰማ ቆም ብላ አሰበች ቢሆንም ስጋዊ መንፈሷ እልህ አሲዟት መንገዷን ቀጠለች ቀጥታም ዶርም ገብታ ማንንም ሳታናግር ተጠቅልላ ተኛች ወይናም ትንሽ ቆይታ ከኋላዋ መጣች ሰአዳና ብርሀን ደነገጡ አንቺ በአላህ ምን ሆነሽ ነው አለቻት ሰአዳ ብርሀንም ቀጥላ አረ ምን ጉድ ነው በማሪያም መቅደስ ነይ እያት ብላ ልትቀሰቅሳት ስትል እንደተኛ ሰው ዝም አለቻት ወይናም ምንም አልሆንኩም አታስቡ ደናነኝ ብላ እሷም ተኛች ሁለቱም እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ሲገላበጡ አደሩ ጠዋትም........
.........መቅደስ ተነስታ ጌዲዮ ጋር ሄደች ተያይዘውም ካፌ ገቡ ምን ሄነሽ ነው ማታ ስደውል ስልክሽን ያላነሳሽው አላት እሷም ዝም አለችው ፊቷ ልክ አልነበረም መቅዲ ምን ተፈጠረ ትክክል አይደለሽም አላት እሷም አዎ
አይደለሁም እንዴ ምን ሆንሽብኝ አላት እሷም የተፈጠረው ነገረችው እሱም እንዴ ታዲያ ይቅርታ ሳታረጊላት መጣሽ አላት ጌዲ ከበደኝ በሷ የተነሳ እኮ እኔና አንተም ተለያይተን ትምህርታችንንም አጥተን ነበር አለችው ጌዲ ፈገግ ብሎ መቅዲ እውነተኛ ፍቅር ይፈተናል በርግጥ አጥፍታለች ግን እኛ ከተፃፈልን ውጪ አልኖርንም አንኖርምም አንዳንዶቻችን የሌላውን ብርሀን ስላጨለምን የኛ ይበልጥ ይበራል ብለን እናስባለን ግን ተሳስተናል ከምንም በላይ ግን ጥፋተኝነትን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅ ጥበብ ነው ይቅርታንም መቀበል መሸነፍ ሳይሆን ትልቅ ብልህነት ነው ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም ፍቅራችንን ገደል ልትጨምረው ብትሞክርም ከገደሉ የመለሰችውም እሷ ነች አላት ግን ይህን የተናገረው እንዳትናገር ያለችውንም የነገረቻት መስሎት ነበር መቅደስ ቀበል አርጋ እንዴት ነው ከገደል የመለሰችው አላት....
ክፍል 23 ይቀጥላል......
ለሀሳብ አስተያየት👉 @Torera1
ለመቀላቀል👇👇
@ethio_fun