💞#ትርታየ💞. #ክፍል 23

የነገረቻት መስሎት ነበር መቅደስ ቀበል አርጋ እንዴት ነው ከገደል የመለሰችው አላት እንዴ የዛቀን ማታ ስልክ ባትደውልልኝ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስበሽዋል በዛላይስ እኔን ለማስፈታት ካገቱሽ ልጆች መረጃ ለመሰብሰብ አንሶላ እስከመጋፈፍ እራሷን ለመስዋት ማቅረቧ ይቅርታን ሊያስደርግላት አይችልም መቅደስ ጭንቅላቷን ያዘች ቆይ ለምን አልነገረችኝም ስትል ጌዲ ደንግጦ አልነገረችሽም እንዴ አላት አዎ ብላ ከመቀመጫዋ ተነስታ ቡሀላ እንገናኛለን ብላው እየሮጠች ሄደች።
.......ዶርም ስትገባ ወይና እያለቀሰች ለመሄድ ሻንጣዋን እያዘጋጀች ነበር መቅደስም ተቆጥታ የት ልትሄጂ ነው አለቻት ወይናም አባቴ ሰው ያስፈልገዋል ልሂድለት አለቻት መቅደስም ውሸትሽን ነው ይቅርታ ስላላረኩልሽ ነዋ አለቻት ወይናን ባታረጊልኝም አልፈርድብሽም ስትላት መቅደስ ጥምጥም ብላ አቀፈቻትና ይቅርታዋን እንደተቀበለቻት ነገረቻት ወይና በደስታ ጮቤ እረገጠች ትልቅ ሸክም ቀለለላት..........
......ከዚህ ቡሀላ ወይና ከመቅደስና ከጌዲዮ ጋር በመተባበር ዮናስን ለፍርድ የሚያበቁ መረጃዎችን ሰበሰቡ ለምሳሌ ሴቶችን ለሹገር ዳዲዬች እንደሚሸጥ አደንዛዥ እፆችን ግቢ ድረስ እንደሚያዘዋውር ሌሎችም ከዛም ከጅማ ዩኒቨርስቲ ግቢ ተባረረ በመቀጠልም በፍርድ ቤት ሶስት አመት ተፈረደበት.......
...... ከዚህን ጊዜ በፍቅራቸው ማህል የገባና ከፍተኛ ክፍተት የፈጠረ ሰው የለም ያመቱ መጨረሻ ላይ ማለትም ትምህርት ሲዘጋ ጌዲዮ መቅደስን ወሎ ድረስ ወስዶ ከናቱ ጋር አስተዋወቃት እናቱም ልክ እንደኔ ሆነሽ ልጄን ተንከባከቢልኝ ብለው አደራ ሰጧት መቅደስም ብትሆን ያለምንም ፍርሀት ቤተሰቦቿ ጋር ወስዳ አስተዋወቀችው ከዛም ሁሉም ቤተሰቦቿ በተሰበሰቡበት በሽታው ተነስቶበት ወደቀ የሚገርመው ግን አንድም ሰው አልተቃወማትም እንደውም ኮሩባት ልጃችን ገንዘብ ቤት መኪና መልክ ቁመና ዝና ሳትል ፍቅርን መረጠች ብለው ልክ እንደጌዲዮ እናት የመቅደስም ቤተሰቦች መረቋቸው እህት ወንድሞቿም ቷናሻችን ብትሆኚም ሁሌ አርአያችን ነሽ ብለው ተራ በተራ እያቀፉ ሳሟት።.. ያው በሽታው ሲብስበት ፀበል ይዛው እየሄደች ታስታምመዋለች እናም በዚህ መልኩ ጌዲዮና መቅደስ ድፍን ሌላ ሁለት አመት በፍቅር ዘለቁ ከሁለት አመት ቡሀላ ምን ሊፈጠር ይችል ይሆን አብረን የምናየው ይሆናል.......
።።።
ዉድ አንባቢዎች ቀጣዩ ክፍል ቶሎ እንዲደርሳችሁ ሼር በማድረግ ሌሎችም ማንበብ እንዲችሉ አድርጉልን! እናመሰግናለን!!
ለሀሳብ አስተያየት👉 @Torera1
ለመቀላቀል👇👇
@ethio_fun