💞#ትርታየ💞. #ክፍል_25

የመቅደስ ድንጋጤ አንደበቷን አሰረው ሰውነቷን አደነዘዘው የምትሆነው ግራ ገባት ብቻ ደጋግማ ጌዲ ጌዲ ትላለች ጌዲዮ ግን አውቆ ስለነበር መጨረሻ ላይ በሳቅ ተንፈራፈረ ወይኔ መቅዲ ብሞትም አትጮሂም ማለት ነው እያለ የማያቋርጠውን ሳቁን ይስቅ ጀመር....በድንጋጤ ብቻ ቢሞት መቅደስ ሞታ ነበር ሞቶ መመለስም እንዲህ ከሆነ መቅደስ ግማሽ መንገድ ሄዳ ነው የመጣችው...እንደምንም እራሷን አረጋግታ እውን ቀልድ መሆኑ ሲገባት ንዴት ፊቷን በርበሬ አለበሰው...እሱ ግን አሁንም ይስቅ ነበር ቀልደህ ልብህ ወልቋል አለችው ጌዲም እየሳቀ እንዲህ ልበቢስ መሆንሽን ባቅ ኖሮኮ እንዲህ አይነት ቀልድ አልቀልድም ነበር ሲላት መቅደስ ቦርሳዋን አንስታ ያዘዘችውም ቁርስ ሳይመጣ ጥላው ወጣች እሱም አረ ቁርሱ ቢቀር ልልበስና አብረን እኔዳለን አላት እሷ ግን እንዳልሰማች ሆና ከንዴቷ ብዛት መሬቱን አጥብቃ እየረገጠች ጥላው ሄደች።.....
.........ከዛም ቡሀላ ደጋግሞ ብዙ ጊዜ ቢደውልላትም ልታናግረው ፍቃደኛ አልሆነችም በመጨረሻም እንደተቀየመችውና እንደማታነሳው ሲገባው ወይንሸት ጋር ደወለ ወይናም ገና ከማንሳቷ አንተ ልጅቱን ምን አርገሀት ነው እንዲህ አደንዝዘህ የላካት ነው ወይስ ድንግልናዋን ዛሬ ነው የወሰድከው ብላ እየሳቀች ጠየቀችው ጌድዮም ባማረው ሳቁ አጅቦ እሱንማ እኮ ቆየሁ ከተረከብኩት ባይሆን ትዝታው ይሆናል አላት ወይናም ሳቁን ተቀብላ እየሳቀች ትዝታ እንዲህ ቢያረግማ እኔ በሽተኛ እሆን ነበር አለችው እሱም ወይናዬ ባክሽ በሆነ ነገር አስቀይሚያት እኮ ነው ስልኳንም አላነሳም አለችኝ በማሪያም አገናኚኝ አላት እሷም ውይ ጌዲዬ ገና ስወጣ ነው የደወልክልኝ አሁን ደግሞ ላይብረሪ ልገባ ነው ባይሆን ብርሀንና ሰአዳ ዶርም ስላሉ አንድኛቸው ጋር ደውል አለችው ......
እሱም መልሶ ሰአዳ ጋር ደወለና እንድታገናኘው ጠየቃት መቅደስ ግን አላናግረውም ስትል ብርሀን ለመነቻትና እሺ አለች ስልኩንም ተቀብላ ምን ፈለክ አለችው ጌዲም መቅዲ እግዚያብሄርን እንዲህ ያስከፋሻል አላልኩም ይቅርታ አርጊልኝ አላት ብዙም ካባበላት ቡሀላ ይቅርታ አረገችለትና ሁሌ የሚገናኙበት መናፈሻ እንደሚጠብቃት ነገራት.....
.......የሚገርም ነው ጌዲዮና መቅደስ ፍቅረኛሞች ከሆኑ በኋላ ብዙ ሴቶች ጌዲዮን ለፍቅር ጠይቀውታል በተለይ አደራ የተባለችው የክፍሉ ተማሪ ተፈታትናዋለች ይኸው ዛሬም ሆን ብላ መቅደስን እየጠበቀ የተቀመጠበት መናፈሻ ድረስ ሄዳ አጠገቡ ተቀመጠች ብዙ ብሏት እንቢ ስላለችው ዞርበይም አላላትም ዝም ብሏት ተቀመጠ እሷም ጌዲ ሰላም ነው አለችው እሱም እግዚያብሄር ይመስገን አላት ይቅርታ መቅደስን እየጠበክ እንደሆነ አውቃለሁ ግን በጣም ስለናፈከኝ ነው የመጣሁት አለች ጌዲዮም በግርምት ፈገግ ብሎ እኔ ናፍቄሽ አላት እሷም አዎ ብላ ተጠግታ እጁን ያዘችው መቅደስ ፊትለፊት አየቻቸው እንዳየቻቸውም ቆመች......
.......ጌዲዮም ቀስ ብሎ እራሱን ያዘ ከዛም ሰውነቱን አንቀጠቀጠው በተቀመጠበት ወድቆ ሲንፈራፈር አደራ ሰቀጠጣት እንኳን ልታነሳው የጨበጡት እጆቿን ተፀይፋ እየጠራረገች ጥላው እየበረረች ሄደች መቅደስ ግን ከመቅፅበት እየሮጠች አጠገቡ ደርሳ ስታቅፈው እየሳቀ ነቃና ወይ የዘንድሮ ፍቅር አለ መቅደስ በድጋሚ ተናደደች ምን ለማለት ነው አለችው እሱ እንዴ እሰቢው ጤነኛ እያለሁ አፈቀርኩክ ናፈከኝ አበድኩልህ ስትል የነበረችው ልጅ ታምሜ ስወድቅ ግን ተፀይፋ ጥላኝ ሄደች ታዲያ ይሄ ፍቅር ነው መቅዲዬ ካፈቀሩ አይቀር እኮ ልክ እንዳንቺ ነው ከነ ሙሉ ማንነት የኔ እናት አንቺኮ ትለያለሽ እኔ ማለት እኮ..... በጆቹ ጉንጮቿን ጨብጦ አይን አይኗን እያየ ቀጠለ....ከድለኞች መሀል አንዱ ነኝ አንቺን የሰጠኝን ፈጣሪ በምን ቃል እንደማመሰግነው አላውቅም ብሎ ጥብቅ አርጎ ግንባሯን ስሞ አቀፋት.....መቅደስም
.....ጌዲዬ እኔም እኮ ያንተ በመሆኔ እድለኛ ነኝ ደግሞ ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ አትቀልድ እኔኮ ህመምክ ያስፈራኛል አለችው እሱም ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ እንደማይቀልድ በፈጣሪ ስም ምሎ ቃል ገባላት ....እንዲህ እንዲህ እያሉ ደሞ ሌላ ወራቶች አሳለፉ............
...ክፍል 26 ይቀጥላል......
ለሀሳብ አስተያየት👉 @Torera1
ለመቀላቀል👇👇👇
@ethio_fun @ethio_fun