💕ትርታየ💞. ክፍል 26. እንዲህ እንዲህ እያሉ ደሞ ሌላ ወራቶች አሳለፉ............

.......ፈተና እየተፈተኑ ስለነበር አሁን በብዛት ጥናት ላይ ናቸው ሰሞኑን ግን ጌዲዮ በጣም እያመመው ነው ቢሆንም ጌዲዮ ህልሙን ለማሳካት ጠንክሮ እየተማረ ነው ዛሬ ደግሞ ከመቅደስ ጋር አብረው ሁሌ የሚያጠኑበት ጫካ ሄደው እያጠኑ ነው ጥናታቸውንም እንደጨረሱ ጌዲዮ የመቅደስ እግር ላይ ተኝቶ እንደለመደው አይናይኗን እያየ ምን እንደናፈቀኝ ታውቂያለሽ አላት እሷም ምንድነው አለችው የምመረቅበት ቀን አላት ውይ አሁንማኮ ጨረስክ ግማሽ አመት እኮ ነው የቀረህ ግን ለምን ጓጓህ ጌድዬ አለችው እንዴ መቅዲ የማዬን ደስታ ለማየት ነዋ የኔን አለም የምታሳየኝ ተምረህ ተመርቀህ ነው ትለኝ ነበር ታዲያ አለሟን ለማሳየት ለምን አልጓጓም አላት መቅደስም ፈገግ ብላ እሱማ መመረቅክ የኔም አለም እኮ ነው ስትለው ግን ምንድነው ስጦታዬ አላት እሷም ያገር ቀይ አበባ ተሸክሜ እሰጥሀለሁ አለችው በቃ አላት እህ ብችልማ ቀይ ምንጣፍም ባስነጥፍልህ ደስ ይለኛል አለችው ጌዲዮም ስቆ ሀሳብሽም በቂዬ ነው የኔ እናት ደግሞ የዛሬ አመት አንቺ ስትመረቂ እኔም በተራዬ በዛ ሁሉ ህዝብ ፊት ተንበርክኬ የኔ እመቤት አግቢኝና የፍቅርሽ ታዛዥ ባሪያሽ ሆኜ እድሜ ዘመኔን ልገዛልሽ እልሻለሁ አላት........
......መቅደስ ዛሬ ላይ ሆና የቀጣዩን አመት ምርቃቷን ቀን በምትወድደውና በምታፈቅረው የጌዲዮ የጋብቻ ጥያቄ አጣምራ ደስታዋን በህሊናዋ ሳለችው ከዛም ጌዲዬ ጊዜ ፊልም ቢሆን አሳልፌ የምርቃቴ ቀን ላይ አርጌው ነበር ብላ ጎንበስ ብላ በስስት ከንፈሩን ሳመችው ደሞኮ ጌዲ የምርቃትህ ቀን መጀመሪያ እኛ ቤት ነው የምንሄደው አለችው ለምን አላት እንዴ እማዬ እኮ እደግሳለሁ ብላለች ከዛም የማዬ ግብዣ እንዳለቀ ብሩክ(ታላቅ ወንድሟ) ይዞን ቀጥታ እናንተ ቤት አለችው ጌዲዮ ደስታው ተደማምሮ እቅፍ አረጋት........
........ከዛም ቀጥታ ግቢ ሄዱ እንደገቡም ትንሽ እንደተራመዱ ጌዲዮ አካባቢው ሁሉ ጨለመበት መቅደስን ጥብቅ አርጎ ያዛትና መቅዲ እራሴን አላት እሷም ደንግጣ ምን ሆንክብኝ አለችው እኔንጃ እራሴን መቅዲዬ ያዢኝ ሁሉም ጨለመብኝ አላት መቅደስ ላንዴ አይኗ በንባ ተሞላ እኔን ምንም አትሆንም ፀሀዩ ይሆናል አለችው ከዛም እንደምንም ብላ ወደጥግ አስቀመጠችውና ክብሪት ልትፈልግ ተነስታ ልትሄድ እጇን ከጁ ልታስለቅቅ ስትል መቅዲ የትም አትሂጂ ደግፊኝ እራሴ ሊፈርስ ነው ብሎ በፍርሀት አጥብቆ ያዛት ምንም ጌዲዮ ሁሌ ቢወድቅም እንዲህ ብሏት ግን አያውቅም አቅፋው ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ሳቅና ደስታቸው ላንዴ በሀዘን ተቀየረ ጌዲዮ እንደምንም ፊቷን ፈልጎ እንባዋን እየጠረገላት መቅዲዬ ጠንካራ ሁኚ እኔኮ ሁሉም ጨለመብኝ አላት የሱም እንባ እየወረደ መቅደስ ላንዴ በለቅሶ ሲቃ ሲጥ አለች ወዲያው የግቢው ሰው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተሰበሰበ ጌዲዮም ወዲያው እራሱን ሳተ የሷም ሆነ የሱ ጓደኞች እያለቀሱ ነበር አብዛኞቹ ግን እንዳለፈው አወዳደቁ የወደቀ መስሏቸው ይነቃል እያሉ ነበር ቢሆንም ለተከቴይ ሶስት ሰአት ቢጠብቁትም ሊነቃ አልቻለም መቅደስ ለሁለት ተይዛለች ብቻ እየቀለደብኝ ነው ውሸቱን ነው እያለች ተንሰቅስቃ ታለቅሳለች ወዲያውኑ አንቡላንሱ እያበረረ ጅማ ጠቅላላ ሆስፒታል አደረሳቸው ወዲያው ዶክተሮቹ ተባብረው ድንገተኛ ክፍል አስገቡት አብረውት የመጡት መቅደስ ሰአዳና በለጠው ብቻ ነበሩ ለነገሩ መቅደስ አለች አትባልም እሷም ለህክምና አልጋ መያዝ እንጂ የቀራት ደንዝዛለች ብቻ በር ላይ አንዴ ቁጭ አንዴ ብድግ እያለች ነው ሌሎቹም ጓደኞቻቸው ተከታትለው እየሮጡ ሴክሬተሪዋን ጠይቀው ያሉበት ክፍል እየሮጡ ደረሱ እንደደረሱም እንዴት ነው አሁን አሏቸው በለጠውም ዶክተሮቹ ገና አልወጡም አላቸው ከዛ ሁሉም በጭንቀት ተከበው መጠበቅ ጀመሩ። ከዛም ቢያንስ ካንድ ሰአት ቆይታ ቡሀላ ዶክተሮቹ ወጡ እንደወጡም ሁሉም ተሯሩጠው ከበቡዋቸው ዶክተር እንዴት ነው አሉ አንዱ ዶክተር ሲቀር ሌሎቹ ፊታቸው ሳይፈታ ጥለዋቸው ሄዱ ሁሉም ፈሩ መቅደስማ አንድኛዋን ተዝለፈለፈች ዶክተሩ ቁና ተነፈሰና ሊያወራ ሲል መቅደስ ዶክተር በፈጠረህ ክፉውን እንዳትነግረኝ ሞተ እንዳትለኝ ስትለው ወይንሸት አረ መቅደስ ሶስት ጊዜ አማትቢ አለቻት ዶክተሩም እ.እ መኖሩን አለ እኛም የተቻለንን እርዳታ አርገንለታል ግን አሁንም ሁሉም ግን ምን አሉት አልነቃም ...
ክፍል 27 ይቀጥላል።
ለሀሳብ አስተያየት👉 @Torera1
Join👇👇
@ethio_fun