#ትርታየ. #ክፍል 27

ዶክተሩም እ.እ መኖሩን አለ እኛም የተቻለንን እርዳታ አርገንለታል ግን አሁንም ሁሉም ግን ምን አሉት አልነቃም የሚያስፈልገውን ህክምና ሰተነዋል ተራ በተራ እየገባችሁ ማየት ትችላላችሁ ከሁለት ሰው በላይ ግን ውስጥ መቀመጥ አይቻልም ሌላው ከታማሚው ጋር ቀረቤታ ያላችሁ ክፍል ቁጥር 24 ቢሮ መታችሁ አናግሩኝ ብሏቸው ሄደ መቅደስ ቀድማ ገባች ስታየው ይባስ ሲጥ እስክትል ድረስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲዮ ከወገቡ በላይ ብዙ ገመዶች ተጠላልፈውበታል አፍና አፍንጫውም በኦክሲጅን መስጫ ታፍነዋል እጆቹም ተዘርግተው አይንቀሳቀሱም ሳቁ ጠፍቶ ከንፈሮቹ ተከድነዋን የሚያምሩት መቅደስን አይተው የማይጠግቡት አይኖቹም ተከድነዋል እጁን ጭምቅ አርጋ ይዛ እየሳመችው ጌዲዬ ፈተና እኮ አላለቀም ደሞስ ላይብረሪ እንገባለን ተባብለን አልነበር ለምን አትነሳነሳም እንሂዳ ጌዲ የው ውሸት አያምርብህም በኔ አትጨክንማ ተው ተነስ እያለች ለማይሰማት ጌዲ ብዙ አወራችው መቆየቷን የተረዱት ጓደኞቻቸው እዛው እያለች እየገቡ ጌዲዮን እግዚያብሄር ይማርህ እያሉ እሷንም እያፅናኑ ወተው ደጅ ላይ ተቀመጡ ከዛም በለጠውና መቅደስ ዶክተሩ ቢሮ ሄዱ ሲገቡም እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ከዛም በለጠው ዶክተር ችግር አለ እንዴ ብሎ ጠየቀው ዶክተሩም እየውላችሁ አሁን እንዲህ ነው ብሎ መናገር ይከብደኛል ምክንያቱም ሙሉ ምርመራ መደረግ አለበት ላሁን ግን ጥያቄዎችን ልጠይቃችሁ ታማሚው ከዚህ በፊት እራሱን ይስት ነበር??...አዎ ግን እንደዛሬው ሆኖ አያውቅም ህክምናስ ተደርጎለት ያውቃል?? መቅደስ ይህን ጥያቄ ለመመለስ አንደበቷን ፈታች ስንቴ እንደለመንኩት እኮ ይኸው ይሄ ቀን እንዳይመጣ ፈርቼ ነበር ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች በለጠው ደግፏት ነበረ ስታለቅስ ግን አቅፎ አባበላት ዶክተሩም ቀጠለ እሺ ያለፈው አልፏል አሁን ማሰብ ያለብን ስለወደፊቱ ነው እናም ለካርድ ላልጋ እንዲሁም ለግዜው ህክምና የሚውል 7ሺ ብር ማስያዝ ይጠበቅባችኋል አላቸው ከዛም እንደወጡ በለጠው መቅዲ እጄ ላይ ምንም ሳንቲም የለም ምን ይሻላል አላት አታስብ እቤት እደውላለሁ ብላ አባቷ ጋር ደወለች ሄ..ሎ..ሄ...ሎ አባ ወዬ መቅዲ ደና አደለሽም እንዴ አዎ አባ ጌዲን አሞት ሆስፒታል ነን ይሄን ያክል አዎ አምስት ሰአት ሊሞላው ነው እራሱን ከሳተ ግን አልነቃም አለችው አሁንም እያለቀሰች ነው አባቷም እራሱን ይዞ በቃ አይዞሽ ምንም አይሆንም አሁን ይነቃል ደሞ ሁላችንም ስራ ነን እህትሽ ግን እረፍት ላይ ስለሆነች አሁን እልካታለሁ እሺ እሺ አባ ብትችል ግን አሁን 7ሺ ላክልኝ አረ እልክልሻለሁ ምንም ችግር የለም ብቻ አንቺ እራስሽን አረጋጊ እሺ አባ አመሰግናለሁ።ጌዲዮ ይነቃል እየተባለ ሲጠበቅ ሳምንት ሞላው የጅማ ጠቅሌ ሆስፒታል ዶክተሮችም የጌዲዮ ነገር ካቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ወደ አ.አ ተክለ ሀይማኖት አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ተፃፈለትና ከጅማ ተነስተው አ.አ ገቡ እስካሁን ያልተነገራቸው የጌዲዮ እናትም በጣም እየደወሉ ልጄስ እያሉ ሲጠይቁ በብዙ ምክንያት መታመሙን ቢደብቋቸውም የወለደ አንጀት ነውና ጌዲ መታመሙን ተረድተው አጥብቀው ሲለምኑ ግድ ሆነባቸውና ዛሬ እውነቱን ተናገሩ አይ እናት በሞት መሀል ሆነው ነው አ.አ የደረሱት ያው እነ ብርሀን በለጠው ወይና ሰአዳ እንዱሁም ሌሎቹም መቅደስ ስትቀር ነገ ፈተና ስላለ ተመልሰው ጅማ ሄደዋል መቅደስንም ቢሆን ቤተሰቦቿ እንዲሁም የጌዲ እናት ሄዳ ፈተናዋን እንድትፈተን እየለመኗት ነው እሷ ግን ካልነቃ አልሄድም አለቻቸው የጌዲዮ እናት ለቅሷቸው መራራ ነው የመንገዱ ድካም ሳይሰማቸው ሰውነታቸው መዛሉ ሳይሰማቸው ልጃቸው እግር ላይ ተደፍተው አሁንም መራራ እንባ እያነቡ ነው መቅደስማ እንባዋ አልቆ ፈዛለ ቡሀላም እንደምንም ለምነው የመቅደስ ቤተሰቦች የጌዲዮን እናት ይዘው እቤት ሄዱ መቅደስ አሁንም አልጋው ላይ በግንባሯ ተደፍታ እያንቀላፋች ነው የሆነ ሰአት ላይ የጌዲዮ ጣቶች ሲንቀሳቀሱ ተሰማትና ከህልሟ እንደነቃች ሆና ባተተች ስታየው አይኖቹ ግራና ቀኝ እያዩ ነው ደስታዋ አንቋት ላንዴ ጮኸች ተጣድፋ ሄዳ ግንባሩን ደጋግማ ሳመችው ከዛም ጌዲዬ ነገ እኮ ፈተና ነው አብረን እኔዳለን አይደል አለችው መንቃቱን ከነርስ የሰሙት ዶክተሮች እየተሯሯጡ መጡ ወዲያው መቅደስ አያችሁ አይደል ዳነ ነቃ እኮ ዶክተር ፍቱለት ነገ ፈተና አለብን እኔዳለን አለቻቸው ዶክተሩም ይቅርታ ወይዘሪት መቅደስ ይህን ማድረግ አንችልም እንዴ ለምን ነቅል ማለት እኮ ዳነ ማለት አይደለም አረ ዶክተር ጌዲኮ ሊመረቅ የቀረው ወራቶች ብች ናቸው...
#ክፍል 28 ይቀጥላል
ለሀሳብ አስተያየት👉 @Torera1
ለመቀላቀል👇👇
@ethio_fun