💕#ትርታየ💞. #ክፍል 28

ዶክተር ጌዲኮ ሊመረቅ የቀረው ወራቶች ብቻ ነው የዚን ሳምንት ፈተና ተፈትኖ የመመረቂያውን እሪሰርች ካላስረከበ አይመረቅም ዶክተር ጌዲ መመረቅ ይፈልጋል እያለች እየለፈለፈች የዶክተሩን ጋውን ጨምቃ ያዘችው ዶክተሩ በተፈጠረው አጋጣሚ አዝኖ አንገቱን ደፋ በእውነት ወይዘሪት መቅደስ ቢወጣና ቢፈተን ደስ ባለኝ ነበር ግን አሁን ይውጣ ማለት በሂወቱ መፍረድ ነው ስለዚህ መውጣት አይችልም ብሏት ሄዱ። የስከዛሬ ህልሙ እናቱን የማስደሰት ምኞቱ ቅዠት መሆኑ አሳዝኖት የጌዲ እንባ በግራና በቀኝ ፈሰሰ መቅደስ ሲያለቅስ ስታየ ጌዲዬ የማትመረቅ መስሎህ ነዋ ዝም በላቸው ትመረቃለህ እሺ ጌዲዮ አፉ ላይ የተደቀነውን ኦክስጂን አነሳና መቅዲ ትወጂኛለሻ አዎ ታፈቅሪኛለሽም ጌዲዬ በጣም ደስታዬስ ደስታሽ ነው እንዴ ምን ጥያቄ አለው እሺ እንደዛ ከሆነ አሁኑኑ ሂጂ ለጠዋት ፈተና እንድትደርሺ አልሄድም መቅዲ ያልሽኝ ሁሉ እውነት ከሆነ ሂጂ አንተ ሳትሄድማ አልሄድም ስሚኝ የሰው ልጅ ያስባል የሚፈፅመው ግን ፈጣሪ ነው እኛ ባለማወቅ አርቀን ብዙ እንመኛለን ባለም ስንኖር ግን ሂወት ትቀያየራለች ስለዚህ እኔ ምንም ብሆን ምንም አንቺ ግን መማር አለብሽ መቅደስ ደግማ አልሄድም ስትለው ጌዲዮ በንዴት መሄድ አለብሽ!!!!! ብሎ ጮኽባት ክው ብላ ቀረች ከዛም በቃ እሺ አትቆጣ እሄዳለሁ ስትል ታላቅ ወንድሟ በሩን ከፍቶ ገባ እንኳን ለዚህ አበቃህ አለው ጌዲዮም ቅዱስዬ አመሰግናለሁ አለው አሁን እንዴት ነህ ደና ነኝ እግዚያብሄር ይመስገን
.......መቅደስና ጌዲዮ በብዙ ፈተና ሶስት አመት በፍቅር አሳልፈው አራተኛው አመት ግን አስጊ ሆኗል ጌዲዮ የጓጓለትን ያምስተኛ አመት ትምህርቱን መጨረስ አልቻለም ዋና የሚባለውም ፈተና አምልጦታል ከሆስፒታ ወጥቶ እንዲፈተን መቅደስ ዶክተሩን ብትለምነውም ለሂወቱ አስጊ ስለሆነ እንደማይወጣ ነግሯት እሷም አልፈተንም ብትልም ጌዲዮ በፍቅሩ ለምኗት ፈተናዋን ለመፈተን ጅማ ተመልሳ ዛሬ ወደ አ.አ መጥታለች ሙሉ የህክምናውን ወጪ ችለው እያስታመሙት ያሉት የመቅደስ ቤተሰቦች ናቸው እናቱም ከክፍለ ሀገር መጥተው አብረውት ነው ያሉት ጌዲዮ ከራሱ በላይ የናቱን ህልም አለማሳካቱ ተስፋ አስቆርጦታል መቅደስም በሱ መታመም ሌት ተቀን እያለቀሰች በድን ብትሆንም ዛሬም ትምህርቱን ቀጥሎ እንደሚመረቅ ተስፋ ትሰጠዋለች.......
......ዛሬ ውጤትህ ይመጣል ስለዚህ ለዩኒቨርስቲው አሳውቀን ብትዘገይም ትፈተናለህ እሪሰርችህንም ቢሆን ትጨርሰዋለህ አለችው መቅደስ የፍርሀትና የደስታ ስሜት እየታየባት የጌዲዮ እናትም እንዳፍሽ ያርገው አሏት የሱዋም አባት እንደዛው ጌዲዮ ግን ውስጡ ጤነኝነት እየተሰማው ስላልሆነ የሚመጣው ውጤት ጥሩ ይሆናል ብሎ መገመት ተስኖታል ብቻ ባጠቃላይ አፋቸው መልካም ቢናገርም ውስጣቸው ፈርቷል ሰአቱ ሲደርስም መቅደስና አባቷ ውጤቱን ለመስማት የዶክተሩ ቢሮ ሄዱ እንዲቀመጡም ከጋበዛቸው ቡሀላ ዶክተሩ ከምን መጀመር እንዳለበት ግራ ገብቶት አይን አይናቸውን ያያቸው ጀመር ውስጣቸው ይበልጥ ተረበሸ ዶክተር ችግር አለ እንዴ አሉት ........
.......እየውላቹ ይህ ዜና ለናንተ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ ግን ግዴታ መናገር ስላለብኝ ስሙኝ ጌዲዮ የጭንቅላት እጢ ታማሚ ነው መቅደስ አፏን ይዛ እየተንቀጠቀጠች ምን አለች አዎ ህክምናውን በጊዜ ጀምሮ መዳኒት ስላልወሰደም በሂወት የመኖር ጊዜውን አጥቦታል መቅደስም ሆነች አባቷ እንባቸው ድንገት እንደሚጥል በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ዱብ ዱብ ይል ጀመር መቅደስ በልህ ድምጿን ከፍ አድርጋ እና ይሞታል ልትለኝ ነው አለችው ዶክተሩም አላልኩም የምትችሉት ከሆነ አንድ እድል አላችሁ አላቸው አባቷ እንደምንም አረጋግቷት ምንድነው ንገረን ብቻ ጌዲዮ ይዳን እንጂ የሆነውን ይሁን ለመፈፀም ዝግጁ ነን አሉ ባስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት መቅደስ አይሆንም ብላ ይበልጥ ጮኸች ችግሯ ህመሟ ቢገባውም መረጋጋት ባለመ
ቻሏ ዶክተሩ ተናደደ መቅደስ አዳምጪኝ ቀዶ ጥገናው እዚህ ሀገር አይሰጥም ይህ ማለት በዚህ አራት ወር ውስጥ ካገር ወጥቶ ቀዶ ጥገናውን ካላደረገ በሂወት መኖሩ አስጊ ነው ለህክምናው ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብሎ ሃሳቡን በቁጣ ገልፆ ቁና ተንፍሶ ላንዴ ዝም አለ መቅደስና አባቷም በህልማቸው እስኪመስላቸው ደርቀው ቀሩ ምንም ሳይናገሩም ቢሮውን ለቀው ወጡ.......... ይቀጥላል......
ለሀሳብ አስተያየት👉 @Torera1
Join👇👇
@ethio_fun