#ትርታየ. #ክፍል 29. ምንም ሳይናገሩም ቢሮውን ለቀው ወጡ..........

......ከወጡ ቡሀላ መቅደስ ተዝለፍልፋ ወደቀች ነርሶችም ተሯሩጠው አንስተው አስተኟት ስትነቃም ሁሉም ቤተሰቦቿ ተሰብስበው ነበር አባቷ ነግሯቸው ስለነበር ሁሉም አይናቸው በንባ ብዛት በርበሬ መስሎ ነበር እማ ሁለት ሚሊዮን ያስፈልጋል አሉ እኮ አለቻት የቤተሰቦቿን አይን አይን እያየች እህቷም እሷን ለማፅናናት ያንቺ እንዲህ መሆን እኮ ብር አይሆንም ይልቅ ብሩን እንዴት ማግኘት እንዳለብን ብናስብ ነው የሚሻለው ስትል እንዴ ከየት ነው የሚመጣው አለች መቅደስ ቀጥሎም ቅብጥብጡ ወንድሟ ሲስቱ ተነካሽ እንዴ ሁለት መቶ ሺ ማግኘት ከባድ በሆነበት ሀገር እንዴት ብለሽ ነው ሳይጨርሰው የሁላቸውም ታላቅ የሆነው በረከት ከየትም ብለን አግኝተን መታከም አለበት እናትየዋም አዎ ቤታችንንም ቢሆን ሸጠን እናሳክመዋለን ማሟያ ደግሞ ሁላችንም አካውንት ያለውን ብር እናወጣለን ካልሞላም ብድር አናጣም የሚል ተስፋ ለመቅደስ ሰተዋት ከዛን ቀን ጀምሮ በየፊናቸው ብሩን ማፈላለግ ጀመሩ ብዙ ወጪ ስላወጡ የሁሉም አካውንት ውስጥ የተገኘው ብር ስድስት መቶ ሺ ብቻ ነበር ቤቱም ያሰቡትን ብር ሊያወጣ አልቻለም........
.........ሌላ ህመም እንዳይሆንበት ስለፈሩ ነገሩን ለጌዲዮ እስካሁን አልነገሩትም እናቱ ግን ቢሰሙም ደጀ ሰላም እየሄዱ ደጅ ከመፅናት ፈጣሪን ከመለመን ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም ዘወትር የመቅደስን ቤተሰቦች ሲያዩ እንዲህም አለ ወይ ይላሉ ጌዲዮንን ለማሳደግ ያዩትን መከራ እሳቸውና ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው እንኳን የባለቤታቸው ዘመዶች የገዛ ቤተሰቦቻቸውም ሰላምታ ሰተዋቸው እንኳን አያውቁም የጌዲዮ እናት ያለፉትን አመታት ሲያስታውሱ ደም እንባ ያለቅሳሉ ቢሆንም ፈጣሪ እንደሰው አይደለም ይኸው እነመቅደስን ሰጣቸው እውነት በዚህ ሰአት ብቸኛ ቢሆኑ ኖሮ ጌዲዮ ነብሱ ባልተረፈች ነበር ግን ሳይደግስ አይጣላም ይባል የለ..........
.......ግን ምንም እንዳሰቡት ገንዘቡን ማግኘት አልቻሉም ቤቱንም የሚገዛ አጡ ቢያገኙም የሚጠሩላቸው ዋጋ ለቤቱም ለህክምናውም አይመጥንም በቲቪና በራዲዮንም ማስታወቂያ ሊያሰሩ ቢጠይቁም የጠየቋቸው ገንዘብ ከባድ ነበር በዛላይ ዶክተሩ ያለው ግዜ አጭር ስለሆነ በፍጥነት ፕሮሰስ መጀመር እንዳለበት እየነገራቸው ነው አሁንማ ሁሉም ተስፋ ቆርጠው የሚገቡበት ጠፍቷቸው ወደፈጣሪ እግዚኦ እያሉ ነው........
.........ሁኔታቸው ግራ ያጋባው ጌዲዮ ቅብጥብጡን ቅዱስ ብቻውን ሲያገኘው ቅዱሴ አለው ወዬ ጌዲ አለው የህክምናውን ውጤት ንገሩኝ ስላቸው ደና ነው አሉኝ ደና ከሆንኩ ለምን አልወጣም ስላቸው አይ ትወጣለህ ይሉኛል ሰሞኑን ደግሞ ሁላችሁም ተረብሻችኋል ምን ሆናችሁ ነው በጭንቀት ማለቄ እኮ ነው ሲለው ያው ቅዱስ እስካሁንም ያላወራው አፉን ይዘውት እንጂ ወሬ የሚባል አይደብቅም እናም ምን ባክህ የጭንቅላት እጢ አለበት ውጪ ሄዶ መታከም አለበት ለዛ ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብለውን ተፍ ተፍ እያልን ነው ብሎ ካልታከመ መሞቱ እንደማይቀርም ፍርጥርጥ አርጎ ነገረው ጌዲዮ ተስፋ ቆርጦ እና እሞታለሁ አለው አረ ላሽ ትታከማለህ ደሞ ቤታችን ሊሸጥ እየተስማማ ስለሆነ እግዚያብሄር ከረዳን ብሩ ይገኛል ጌዲዮ ከመቅፅበት ህመሙ ተነሳበት.........
ወዲያው ዶክተሮቹ ተሯሩጠው ህክምና አደረጉለት ብዙም
ሳትቆይ መቅደስ መጣች መታመሙን ስታይ ወዲያው ቅዱስ
እንደነገረው ገባትና አንተ ነገርከዋ አለችው ወንድሟ ቅዱስም
መቅዲ ሙች ጠይቆኝ ነው ሲላት አረ ነው እንዴ ድሮም
ጥፋተኛዋ እኔ ነኝ አንተን ሰው ብዬ አምኜህ መሄዴ አሁን ላባ
ሳልናገር ቀጥ ብለህ ውጣ አረ መቅዲ በጥፊ ያላልኩህም
ታላቄ ስለሆንክ ነው ቆይ ቢሞትስ አታስብም እንዴ ስትለው እሺ
ይቅርታ አርጊልኝ ሁለተኛ አይደግመኝም አላት ሁሌ እንዲህ
ትላለህ ግን ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነህ ስትለው እንደምንም
አግባብቷት ይቅርታዋን አገኘ....
......ጌዲዮ ሲነቃ መቅደስ እጆቹን ተንተርሳ ተኝታ ነበር ከዛም
እጁ ሲንቀሳቀስ ነቃች አይኖቿን በንባ ሞልታ ጌዲዬ ደናነህ
ስትለው መቅዲ እሞታለኋ አላት መቅደስ ደንዝዛ ማነው ያለው
ደሞስ ቢሉስ ሰው ፈጣሪ ነው እንዴ አትሞትም ተጋብተን ልጆች
ወልደን አርጅተን ነው የምንሞተው ጌዲዬ ትተኸኝ አትሞትም
ብላ እያለቀስች ፊቱን እየተሽከረከረች ሳመችው ጌዲዮ አለቀሰ
መቅዲ ታቂያለሽ ሁሌ ከንቅልፌ ስነሳ እንደሚጥለኝ
እንደምወድቅ አቃለሁ ግን አንድም ቀን እንኳን እሞታለሁ ብዬ
አስቤ አላውቅም .....
ክፍል 30 ይቀጥላል
ለሀሳብ አስተያየት👉 @Torera1
ለመቀላቀል👇👇👇
@ethio_fun