🌹#ትርታየ🌹. #ክፍል 30. መቅዲ ታቂያለሽ ሁሌ ከንቅልፌ ስነሳ እንደሚጥለኝ

እንደምወድቅ አቃለሁ ግን አንድም ቀን እንኳን እሞታለሁ ብዬ
አስቤ አላውቅም መቅደስ ተስፋዋ ተሟጦ ጮኸችበት ጌዲዮ
አትሞትም አትሞትም ብላ እያለቀስች ትታው ወጣች........
.......ወዲያውም ባስ ይዛ ቀጥታ ጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው
አስተዳዳሪ የዲን ቢሮ ሄደች እንባዋ ያለማቋረጥ ይፈስ ነበር
ሰውነቷ ከስቶ አይኗ ጎርጉዶ ጉንጯ ሟምቶ በተስፋ ማጣት
ተጎሳቁላ ጭራሽ መቅደስ አትመስልም አስተዳዳሪው ደንግጦ
መቅደስ አላት አዎ መቅደስ ነኝ የኔ እንደዚህ መሆን ገረመህ
አዎ ሊገርምህ ይችላል ምክንያቱም አባይን ያላየ ምንጭ
አመሰገነ ጌዲን አላያችሁትማ ካልጋ ተጣብቆ ሞቱን
እየተጠባበቀ ነው አያችሁ የዚህን ዩኒቨርስቲ ስም አራት አመት
ሙሉ አስጠራ ዘንድሮ በመመረቂያው ሲጠፋ ግን ምን ሆኖ ነው
እንኳን አላላችሁትም እሱ ባመጣው ውጤት ለስማችሁ
ለማስጨብጨብ ግን አንደኞች ናችሁ አስተዳዳሪው እንደምንም
አረጋግተዋት ስለተፈጠረው ነገር ለመረዳት ጠየቋት እሷም
ሁኔታውን በሙሉ በዝርዝር ነገረቸው ከዛም የዩኒቨርሲቲው
ኮሚቴዎች ሰብስበው መልስ እንደሚሰጧት ነግረዋት ወጣች
ስትወጣ ወይንሸትና በለጠው አንድላይ እየሄዱ አገኟት
ስለጌዲዮ ሲጠይቋት ሁሉንም ነገረቻቸው ከዛም ተመልሳ አ.አ
መጣች.................
...........ከዛም ጉዋደኞቻቸው እንዳቅማቸው ገንዘብ ማሰባሰብ
ጀመሩ የዩንቨሪስቲው አስተዳዳሪ እንዳሉት ተሰብስበው አንድ
ሀሳብ ላይ በመድረስ ዩኒቨርስቲው ማስታወቂያ ለቀቀ በዚህም
የተነሳ ቤታቸውም ሳይሸጥ ሌላም ከባድ ወጪ ሳያወጡ
የጌዲዮን ሙሉ ህክምና ወጪ የሚችል እስፖንሰር ተገኘ........
......ወዲያውም መቅደስ ጋር ተደውሎ የምስራቹ ተነገራት
ሁሉም ተስፋ በቆረጠበት ሰአት አዲስ ተስፋ በእውነት ደግማ
የተወለደች ያክል ነው የተሰማት ደስታዋንም ለሁሉም አጋርታ
አንድ ላይ ጮቤ እረገጡ ....።
......ዶክተሩም ጋር ሄዳ ገንዘቡ ተገኘ ይድናል አይደል አለችው
መቅደስ ይድናል ብዬ ተስፋ እንጂ እውነታውን ልነግርሽ
አልችልም ምክንያቱም ጌዲዮ የመጨረሻ ከፍተኛውን ቀዶ ጥገና
ነው የሚያደርገው ለዚም ካስር ወር እስከ አንድ አመት
በህክምና ሊቆይ ይችላል አላት የዶክተሩ ንግግር ደስታዋን
ቢያደፈርሰውም ለዚህ ያበቃን ፈጣሪ ነገንም አይጥለንም ብላ
ተስፋዋን ፈጣሪን አደረገች......
አብሮት ለማስታመም ማን መሄድ እንዳለበትም አባቷና እናቷ
ሲጠይቁ መቅደስ እኔ ነኛ አለች ቅዱስ እንዴ አንቺማ አትሄጂም
ልታስታምሚው ነው ወይስ በለቅሶ ልትደፊው መቅደስ ተናዳ አረ
ባክህ ስትለው እህቷም ብሩክም ሁሉም እሷ መሄድ እንደሌለባት
እና የጌዲዮን ቃል ለማክበር መማር እንዳለባት ነገሯት ከዛም
እኔ እኔ በሚል ክርክር ብዙ ከቆዩ ቡሀላ ብሩክ እንዲሄድ ተወስኖ
ፕሮሰሱ ተጀመረላቸው........
........ከዛም የበረራው ቀን እቤት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ሁሉም
ዘመድ ጓደኛ ተሰብስቦ ቤቱ በንባ ታጠበ ጌዲዮ እቤት የመጣው
ባልጋ እየተገፋ ነው ቀና ብሎ እንኳን ቻው ሊላቸው አልቻለም
ነበር መቅደስማ ደግማም የማታየው እየመሰላት ነው በተለይ
ዶክተሩ በቀዶ ጥገና ወቅት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት
ከባድ ነው ያላት ትዝ ብሏት ለቅሶዋ እርም የምታወጣ ነበር የሚመስለው...........
...ክፍል 31 ይቀጥላል
👉Share 👉share 👉share
@Ethio_fun
@Ethio_fun
ለአስተያየትዎ @Torera1