ብሶቴን በግጥም
@weyo_poems

የመወያያ ግሩፕ https://t.me/joinchat/EV-HZUl59e45Ur6gYCJUxQ we present ብሶታችንን using ግጥም @bsoten_begtm_bot ፩. Post እንዲደረግላቹ ምትፈልጉት ግጥም ለመላክ ፪. ይሄ ይሻሻል ይሄን ደሞ ቀጥሉበት ለማለት ፫. ርዕስ ለመስጠት @bsoten_begtm_bot
214  
ብሶቴን በግጥም
2019-06-13 

✍Behar. ቁጣሽ ህመም ነው፡ይቅርታሽ መድሀኒት. ፈገግታሽ ደስታዬ ሀዘንሽ የኔ ሞት. ስልሽ ዝም ብለሽ እያዘን ጠዋት ማታ

ገድለሽ ለማሳየት ለኔ እንደሌለሽ ቦታ
ሞክረሽ ሞክረሽ ባይሳካ
ልብሽ በማዘኑ ቢመካ
አይሆንም እንዳሰብሽው አትልፊ
ሀዘን ለምዶሽ ህመም እንዳታተርፊ
ለፈለገ ያንቺን ደስታ
ሊሰብር ለወደደ ያንቺን ዝምታ
መንገድ ለጠረገልሽ እንቅፋት አትሁኚ
መጣል፡መጠላት አለና ሲወዱሽ አመስግኚ
ይሄን ስልሽ ግን
ሰው የጣለው ይረሳል
ያደነቀው ይነግሳል
ማለት እንዳልሆነ
ልብሽ አይጠፋው፡በፈጣሪ ካመነ
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-13 

እብድ የጻፈው ግጥም. የፈረሰው ቤቴ ቤት መምታት ጀመረ. ሚንቀጠቀጥ እጄ ለቃላት ተጨንቆ አስጊጦ ሰደረ. በግለትሽ ንዳድ የቀለጠች ነብሴ

ዝምታን የሚያውቀው ኮልታፋ ምላሴ
ይ....ቀ....በ....ጣ....ጥ....ራ....ል
ስላንቺ ለመጻፍ ያወጣል ያወርዳል
ከዳህላክ አማልክት አጥብቆ ይለምናል
ትንሿ ዝግ ልቤ ፍቅርሽን ጸንሳ
ዘውትር ማማጥ ብቻ ሆኖ እጣ ክፍሏ
ታምጣለች ሲሻት ትጠበባለች
የፍቅርን ጥግ ለመጻፍ ሐረግ ትሰካለች
ብእር ታስጨንቃለች ብራና ላይ ትጽፋለች
ት..ቸ..ከ..ች..ካ..ለ..ች ...
እናም የኔ እብደት
ልልሽ የፈለኩት ደራሲ ሆኛለው
ይኸው አንገቴ ላይ ሻርብ ጠምጥሜያለው
ቤት የሌለኝ እኔ ቤት ደመድማለው
ይኸው ባንቺ ምክንያት ገጣሚ ሆኛለው
እናም የኔ እብደት ... ካንቺ ጋር መኖርን
በፍቅራችን ፈረስ ሽምጥ መጋለብን
አንቺ እስክትመጪ ከጎኔ እስክቶኚ ጸሐይን ማቆምን
ጊዜን ማወናበድ ትርምስምሱን ማውጣት ልቤ ይፈልጋል
ሎሩሃማ ሆኖ የፍቅርን ምህረት ካንቺ ይማጸናል
አንቺ ግን ... አንቺ ግን እብደቴ ግራ ተጋብተሻል
ወይ አልሄድሽ ወይ አልመጣሽ እመሃል ቆመሻል
የናፈቀሽ ልቤን በደመና ተስፋ እምነት አሲዘሻል
ትመጫለሽ ብሎ ደጅ ደጁን ያያል
እንድትመጪለት ከዳህላክ አማልክት አጥብቆ ይለምናል
የአብዶችን ቅኔ በዜማ ይቀኛል
የቅኔው ሰመመን አንቺን ያስመኘዋል...
✍(በፀጋው)
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-12 

#ለፍቅሬ. #ከትራምፕ. ሐሳቡ የመከነ ተነቦ የሚረሳ ግጥም እፅፋለው. በሞኙ ልቤ ላይ እሷን እስላለው. አንባቢ ተገርሞ...

ተነቦ 'ሚረሳ ግጥም ትፅፋለህ
በሞኙ ልብህ ላይ እሷን ታፈቅራለህ
ሰነፍ ሆነህ ሳለህ ስንኝ የቋጠርከው
በሙኙ ልብክ ላይ ፍቅር የጨመርከው
አይባልም እንጂ ከተባለስ አይቀር ደነዝስ አንተን ነው
ብሎ ይስቅብኛል
ሲስቅ እስቃለው
ስድቤን እውጣለው
በሳቁ ገፍቼ
እኔስ ደንዣለው ውዴ አንቺን አይቼ።
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-10 

✍rozina😛😘😘. ብለው ሲጠይቁኝ ምኞትሽ ምንድነው. ባል ሊያመጡ ምርጫዬን ፈልገው. እኔ ካንተውጪ ማንን እመኛለው

ውዱ ፍቅረኛዬን እኔ እወደዋለው
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-09 

ሕይወቴ. ከውልደት እስከ ስጋ ሞት. ከዝንታለማዊ የብርሀን ሙላት. አውጥተሽ ተራራ ታወርጅኝ ቁልቁለት

የአፍታ ብልጭታ ሆነሽኝ ጥያቄ
.......
ጊዜ መልስ ስጪኝ አልገባኝ ኑረቴ
ከቁሳዊው ኑረት ማዶ ያለዉን እውነት
መገንዘብ ሲያቅትህ ሆኖ የድካም ምት
የገባው ሲስልሽ ያልገባው ሲያልምሽ
.........
ይደናበራል በጧፍ በጠራራ ፀሀይ
አንድ አንቺ ነሽ ህይወት ለካ ምልአት ነሽ
ፍለጋዬም ይብቃና ጎራ ልበል በይኝ
የመሆን ሁሉ መሆኛ ህይወቴ ተረጂኝ...🙁☹😔😔
🔺🔺🔺🔺
✍ናትናኤል
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-07 

✍Beamlak. የቅርቡን ከሩቅ. ላይ ብራቀቅ. የቅርቡን ሳይ ሲርቅ. ላቀርበው ስዳረቅ. የቀረበም ጠፋ. የራቀም ተገፋ

የኔን ልብ ከኔ
የሚያስታርቅ ሲጠፉ።
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-06 

✍Kidi.T. ልጠጣው ልጋተው ከአረቄው ከሜንቱ. ላቡነው ሺሻውን ሣይቀረኝ ከጫቱ. ከዛች ጠባብ ቤት ውሥጥ እንዲያው ቁጭ ብዬ

በሢጋራው ጭሥ ከንፈሬን ተኩዬ
ደሞዝ የማይኖረው የቀን ሥራ ይዤ
ቀጭ ብያለሁኝ የሞት ቀን አርግዤ
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-06 

°°° ዴ ጃ ቩ °°°. ዴጃቩ:-ህልም ቃልበቃል ድርጊትበድርጊት በነባራዊው አለም ሲደገም ወይም እውን ሲሆን የሚሰጠው ስያሜ ነው።

✍ ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ
ከግንቦቷ ማርያም ከ፩ ቀን በፊት
አየሁኝ አንድ ህልም አየሁኝ አንድ እውነት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በቀኒቱ ጠዋት ፀሐይ አልወጣችም
ቀስተደመናዋ በፀሐይ ብርሐን ከቶ አልደመቀችም!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በቀኒቱ ቀን ላይ መሬት ተናወጠች
ቀስተደመናዋም በጭጋግ ጥላሸት ድንገት ተሰወረች!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በቀኒቱ ማምሻ ቀስተደመናዋ በኮከብ 'ረከሰች
የማርያም መቀነት ከማርያም ወገብ ላይ የዛን ጊዜ ወደቀች!
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-03 

ሄዋኔ. የሌለሽን ውበት ጨምሮልሽ ዐይኔ. የሌለሽን ጠረን ሰቶሽ አፍንጫዬ. ግን አልገባሽም እኔ. አንቺን መውደዴ. ስላንቺ ታምሜ

በፍቅርሽ ማበዴ
በሌለሽ ውበት የኔ ቆንጆ
ሞናኒዛ ስልሽ
በሌለሽ ቁመት ቁመተ ሎጋነሽ
ብዬ ሳሞግስሽ
ፀጉርሽ እንኳ ከወገብሽ ሳይደርስ
አቤት ርዝመቱ ብዬ እኔ ስልሽ
ለምን ይመስልሻል እንዲ
አንቺን ማሞግስሽ
ልቤ ታውሮ እንጂ ተይዞ
በወጥመድሽ
ሁሌ ጠዋት ማታ ሀሳቤ
ብዬ ያልኩሽ
ሰለሞንሽ ልሁን ሳባዬ ሁኚ ብልሽ
መች ሰማሽኝ
ህመምሽን ልታመም ብልሽም
ገፋሽኝ
እንግዲያውስ ውቤ የልቤ ትርታ
ሀሳብሽን አልንቅም
ከቃልሽ አልወጣም
አምላክ ለኔ ካለሽ ሄዋኔ ከሆንሽ
የትም አትሄጂም ያው እኔ ጋር ነሽ
ለኔ ከተፃፍሽ ዞረሽ ትመጫለሽ ----------------------------------------- ከ ✍መቅደስ (ye enatye)
ከቱሉ ቦሎ
@weyo_poems
ብሶቴን በግጥም
2019-06-02 

✍ቤተል. *ስትናፍቀኝ*. ቅዳሜ ቀደመ ከእሁድ በፊት፤. እኔ አንተን ሳስብ ሆኜ በፅልመት፤. ሣታንኳኳ ገብተህ ከልቤ ዘልቀህ፤

ምነው ብተኛበት ውዴ በመላህ፤
እኔ አንተን ሳስብህ.....
ጨረቃዬን ትቼ ፀሀይን ዘንግቼ፤
ሁሉን ረስቼ አንተን ብቻ አይቼ፤
ብቻ ስትናፍቀኝ....
መውደዴ ነግሶኝ ፍቅርህ ይናፍቀኛል፤
ምናቦቼ ወተው የታል እርሱ ይሉኛል፤
መልክህ ካጠገቤ የሆነ ይመስለኛል፤
ደግሞ የሣቅ ድምፅህ ይቀሠቅሰኛል፤
ታዲያ ፍቅሬ እንዳልከኝ ስትናፍቂኝ አንቢ
ካምሮዬ ቀድመው የአይኖቼ ግቢ፤
ቃልህን አክብረው ሆኑልኝ የልቤ አብሳሪ
ልቤም ደግሞ ይላል ተይ አንቺ ልጅ ፍሪ፤
ፍቅር ምን ሊረባ ሆድሽን ሊያባባሽ፤
ናፍቆት ምን ሊረባሽ ለጥቆ ሊያስነባሽ፤
በእንባ ጎርፍ ብዛት፤
የልብሽ ስብራት፤
ያበቃ ይመስልሻል?፤
ጠጋኝ በሌለበት ምን ያኳትንሻል፤
ሁሉ ሠባሪ ነው የሣመውን ነካሽ፤
ታዲያስ ይህ ምን ሊረባሽ፤
ተይው አትናፍቂው ይለኛል ደጋግሞ፤
ልቤ እውነታውን መቀበል አቁሞ፤
የብዕሬ ቀለም መሆንክን ረስቶት፤
የምናቤ ምስል እንደሆንክ ዘንግቶት፤
ያልተነካ አምሮዬ የልቤን ስብራት፤
ሀዘንና እንባዬን ህመሜን ረስቶት፤
ዳሩ ግን
ልቤ መናፈቁን ፈፅሞ አይከዳኝም፤
እውነቱን ልንገርህ እኔም አልክድህም፤
ናፍቆቴ አይሎ ፍቅርህ ሲፀናብኝ፤
ርዕሴ አረኩህ ብዬ ስትናፍቀኝ።
ላንተው ነው😘😘
@weyo_poems